ዘፀአት 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ሀገር ላይ እጅህን ዘርጋ፤ አንበጣም በምድር ላይ ይወጣል፤ ከበረዶውም የተረፈውን የምድር ቡቃያ ሁሉና የዛፉን ፍሬ ሁሉ ይበላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአንበጣ መንጋ ምድሪቱን እንዲወርር ከበረዶ የተረፈውን ሁሉና በማሳም ላይ የበቀለውን ሁሉ ጠርጎ እንዲበላ እጅህን በግብጽ አገር ላይ ዘርጋ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን፦ “አንበጣዎቹ በግብጽ ምድር ላይ እንዲመጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ እጅህን በግብጽ ምድር ላይ ዘርጋ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሙሴን “አንበጦችን ለማምጣት እጅህን በግብጽ ምድር ላይ ዘርጋ፤ እነርሱም መጥተው ቡቃያውን ሁሉና ከበረዶ የተረፈውን ተክል ሁሉ ይበላሉ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን “በግብፅ አገር ላይ እንዲወጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ ስለ አንበጣዎች በግብፅ አገር ላይ እጅህን ዘርጋ፤” አለው። |
የምድሩንም ፊት ፈጽሞ ሸፈነው፤ ሀገሪቱም ጠፋች፤ የሀገሪቱን ቡቃያ ሁሉ ከበረዶውም የተረፈውን፥ በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በላ፤ ለምለም ነገር በዛፎች ላይ፥ በእርሻውም ቡቃያ ሁሉ ላይ በግብፅ ሀገር ሁሉ አልቀረም።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ውሰድ፤ በግብፅ ውኆች፥ በወንዞቻቸው፥ በመስኖዎቻቸውም፥ በኩሬዎቻቸውም፥ በውኃ ማከማቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆናል፤” በግብፅም ሀገር ሁሉ በዕንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።