ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
መክብብ 6:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአላዋቂ ይልቅ ለጠቢብ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሕያዋን ፊትስ መሄድን ለሚያውቅ ለድሃ ጥቅሙ ምንድር ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢብ ከሞኝ ይልቅ ምን ብልጫ አለው? ድኻስ በሌሎች ፊት እንዴት እንደሚኖር በማወቁ፣ ትርፉ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበበኛ ከአላዋቂ ምን የተሻለ ጥቅም ያገኛል? ሕይወትን መምራት የሚያውቅ ድሀስ ምን ይጠቀማል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ጥበበኛ ሰው ከሞኝ የሚሻልበት ምን ነገር አለ? ለድኻስ ሕይወትን ለመምራት መቻሉ የሚያተርፍለት ጥቅም ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰነፍ ይልቅ ለጥበበኛ ጥቅም ምንድር ነው? በሕያዋን ፊትስ መሄድ ለሚያውቅ ለድሀ ጥቅሙ ምንድር ነው? |
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።