Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጥበበኛ ከአላዋቂ ምን የተሻለ ጥቅም ያገኛል? ሕይወትን መምራት የሚያውቅ ድሀስ ምን ይጠቀማል?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጠቢብ ከሞኝ ይልቅ ምን ብልጫ አለው? ድኻስ በሌሎች ፊት እንዴት እንደሚኖር በማወቁ፣ ትርፉ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ታዲያ፥ ጥበበኛ ሰው ከሞኝ የሚሻልበት ምን ነገር አለ? ለድኻስ ሕይወትን ለመምራት መቻሉ የሚያተርፍለት ጥቅም ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለጠ​ቢብ ጥቅሙ ምን​ድር ነው? በሕ​ያ​ዋን ፊትስ መሄ​ድን ለሚ​ያ​ውቅ ለድሃ ጥቅሙ ምን​ድር ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከሰነፍ ይልቅ ለጥበበኛ ጥቅም ምንድር ነው? በሕያዋን ፊትስ መሄድ ለሚያውቅ ለድሀ ጥቅሙ ምንድር ነው?

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 6:8
9 Referencias Cruzadas  

በከንፈሩ ከሚወሳልት ሰነፍ ይልቅ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ በጌታ ትእዛዛትና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ ይመላለሱ ነበር።


ጥቂትም በላ ብዙ፥ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ የሀብታም ጥጋብ ግን እንቅልፍን ይከለክለዋል።


በሕያዋን አገር በጌታ ፊት እሄዳለሁ።


ነቀፋ በሌለበት መንገድን እጓዛለሁ፥ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ።


አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ ጌታ ለአብራም ተገለጠለትና፦ “እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፥ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፥


በዐይን ማየት በምኞት ከመቅበዝበዝ ይሻላል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios