Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 6:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ታዲያ፥ ጥበበኛ ሰው ከሞኝ የሚሻልበት ምን ነገር አለ? ለድኻስ ሕይወትን ለመምራት መቻሉ የሚያተርፍለት ጥቅም ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጠቢብ ከሞኝ ይልቅ ምን ብልጫ አለው? ድኻስ በሌሎች ፊት እንዴት እንደሚኖር በማወቁ፣ ትርፉ ምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጥበበኛ ከአላዋቂ ምን የተሻለ ጥቅም ያገኛል? ሕይወትን መምራት የሚያውቅ ድሀስ ምን ይጠቀማል?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለጠ​ቢብ ጥቅሙ ምን​ድር ነው? በሕ​ያ​ዋን ፊትስ መሄ​ድን ለሚ​ያ​ውቅ ለድሃ ጥቅሙ ምን​ድር ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከሰነፍ ይልቅ ለጥበበኛ ጥቅም ምንድር ነው? በሕያዋን ፊትስ መሄድ ለሚያውቅ ለድሀ ጥቅሙ ምንድር ነው?

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 6:8
9 Referencias Cruzadas  

በንግግሩ ከሚቀላምድ ሞኝ ሰው ይልቅ በቅንነት የሚኖር ድኻ ሰው ይሻላል።


የዚህ ዓለም ሀብታሞች እንዳይታበዩ ወይም ተስፋቸውን አስተማማኝ ባልሆነ ሀብት ላይ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፤ እንዲሁም ተስፋቸው እኛን ደስ እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን እዘዛቸው።


ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ የጌታንም ትእዛዝና ሥርዓት ያለ ነቀፋ ይጠብቁ ነበር።


ሀብት ሲበዛ በዚያው መጠን በላተኛው ይበዛል፤ ታዲያ፥ አይቶ ከመደሰት በቀር ለባለቤቱ ምን የሚተርፈው ነገር አለ?


ስለዚህ ሕያዋን በሚገኙበት በእግዚአብሔር ፊት እኖራለሁ።


ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? ከቤተሰቤ ጋር በቅንነት እኖራለሁ።


አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤


ለምኞት ከመገዛት ይልቅ ባለ ነገር መርካት ይሻላል፤ ይህም ደግሞ ከንቱና ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios