መክብብ 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በልቡ ደስታ ስለሚያደክመው እርሱ የሕይወቱን ዘመን ሁሉ እጅግ አያስብም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ የልብ ደስታ ስለሚሰጠውም በሕይወቱ ዘመን ያሉትን ቀናት እምብዛም አያስባቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በዚህ ሁሉ የልብ ደስታን ስለ ሰጠው በዕድሜው ማጠርና መርዘም ከመጠን በላይ አይጨነቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በልቡ ደስታን ስለ ሰጠው እርሱ የሕይወቱን ዘመን እጅግ አያስብም። |
አምላክህንም እግዚአብሔርን ታመልካለህ፤ እኔ እህልህንና ወይንህን፥ ውኃህንም እባርካለሁ፤ በሽታንም ከአንተ አርቃለሁ።
በቸርነትህ የሚታገሡ መንገድህንም የሚያስቡ ይገናኙሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጣህ፤ እኛም ኀጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።