እርሱም ከኤውላጥ አንሥቶ በግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከ ሴይር ባለው ሀገር ኖረ፤ ወደ አሦርዮንም ደረሰ፤ እንዲህም ከወንድሞቹ ሁሉ ፊት ተቀመጠ።
መክብብ 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፤ ሁሉ ከአፈር ተገኘ፥ ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ፤ ሁሉም ከዐፈር እንደ ሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፥ ሁሉም ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውም ሆነ እንስሳ ሁለቱም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ፤ ይኸውም ከዐፈር የተሠሩ በመሆናቸው ወደ ዐፈርነት ይመለሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፥ ሁሉ ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል። |
እርሱም ከኤውላጥ አንሥቶ በግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከ ሴይር ባለው ሀገር ኖረ፤ ወደ አሦርዮንም ደረሰ፤ እንዲህም ከወንድሞቹ ሁሉ ፊት ተቀመጠ።
ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ አፈርም ትመለሳለህና።”
ሰው የሕይወቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕይወት የሚኖር ቢሆን ዳግመኛ እስክወለድ ድረስ፥ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
ወደ ግብዣ ቤትም ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ ይህን መልካም ነገር በልቡ ያኖረዋል።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።