መክብብ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በልቤ፥ “ና በደስታም እፈትንሃለሁ፥ እነሆ፥ መልካምንም እይ” አልሁ፤ ይህም እነሆ፥ ከንቱ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በልቤ፣ “መልካም የሆነውን ለማወቅ፣ በተድላ እፈትንሃለሁ” አልሁ፤ ነገር ግን ያም ከንቱ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ በልቤ እራሴን እንዲህ አልኩት፦ “ና ደስታን በማቅመስ ልፈትንህ፥ መልካምንም ቅመስ፤” ይህም ደግሞ እነሆ ከንቱ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሴን ለማስደሰትና የደስታንም ትርጒም መርምሬ ለማወቅ ወሰንኩ፤ ነገር ግን ይህም ከንቱ ሆኖ አገኘሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ በልቤ፦ ና በደስታም እፈትንሃለሁ፥ መልካምንም ቅመስ አልሁ፥ ይህም ደግሞ እነሆ ከንቱ ነበረ። |
የሶርያም ንጉሥ ንዕማንን፥ “ሂድ፥ ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልካለሁ” አለው። እርሱም ሄደ፤ ዐሥርም መክሊት ብር፥ ስድስት ሺህም ወቄት ወርቅ፥ ዐሥርም መለወጫ ልብስ በእጁ ወሰደ።
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
ዐይኖቼ ከፈለጉት ሁሉ አላጣሁም፥ ልቤንም ከደስታ ሁሉ አልከለከልሁትም፤ ልቤ በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና፤ ከድካሜም ሁሉ ይህ ዕድል ፋንታዬ ሆነ።
እኔም በልቤ፥ “አላዋቂን የሚያገኘው እንዲሁ እኔንም ያገኘኛል፤ እኔም ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ?” አልሁ፤ የዚያን ጊዜም በልቤ፥ “ይህ ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ፥ አላዋቂ በከንቱ መናገርን ያበዛልና።
ከሚበላውና ከሚጠጣው፥ ደስም ከሚለው በቀር ለሰው ከፀሓይ በታች ሌላ መልካም ነገር የለውምና እኔ ደስታን አመሰገንሁ፤ ይህም ከፀሓይ በታች ከድካሙ እግዚአብሔር በሕይወቱ ዘመን ለእርሱ የሰጠው ነው።
አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለብዝበዛም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፤ ለመራገጫም ይሆናል።
እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ነበልባል ከፍ ያደረጋችሁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ብርሃንና ባነደዳችሁት ነበልባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆንባችኋል፤ በኀዘንም ትተኛላችሁ።
ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ።
እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
አሁንም “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን፤ በዚያም ዓመት እንኖራለን፤ እንነግድማለን፤ እናተርፍማለን፤” የምትሉ እናንተ! ተመልከቱ፤ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና።