መክብብ 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንደ ሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጧት ላይ ዘርህን ዝራ፤ ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ፣ ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣ የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጧትም ሆነ ማታ ዘር መዝራትህን አታቋርጥ፤ ሁሉም ይበቅል ወይም አይበቅል እንደ ሆነ የትኛው አዘራር እንደሚሻል ለይተህ ማወቅ አይቻልህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው። |
ይህን ሁሉ በአንድነት ለልቤ ሰጠሁ፥ ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ ልቤ ተመለከተች፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም፥ ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ብዙ ዝናምና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፥ ምድርን እንደሚያረካት፥ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፥ ዘርን ለሚዘራ፥ እህልንም ለምግብ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፥
ለእናንተ ጽድቅን ዝሩ፤ የሕይወት ፍሬን ሰብስቡ፤ የጥበብንም ብርሃን ለራሳችሁ አብሩ፤ የጽድቃችሁ መከር እስኪደርስ እግዚአብሔርን ፈልጉት።