Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ይህን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ለልቤ ሰጠሁ፥ ጻድ​ቃ​ንና ጠቢ​ባን ሥራ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ ልቤ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያ​ው​ቅም፥ ሁሉ ወደ ፊታ​ቸው ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በአምላክ እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጻድቃንና ጠቢባን፥ ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅርም ሆነ ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም፤ ሁሉም በፊታቸው ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ስለ ነዚህ ሁሉ ነገሮች ለረጅም ጊዜ በብርቱ ካሰብኩ በኋላ የደጋግና የጥበበኞች ሰዎችን ሥራ በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆነ ተረዳሁ፤ ስለዚህ ወደፊት የሚገጥመውን ነገር ፍቅርም ሆነ ጥላቻ አስቀድሞ የሚያውቅ ሰው የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 9:1
31 Referencias Cruzadas  

ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ላ​ቸው፤ ቅዱ​ሳን ሁሉ ከእ​ጅህ በታች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም የአ​ንተ ናቸው። ቃሎ​ች​ህ​ንም ይቀ​በ​ላሉ።


ከፀ​ሓይ በታች በም​ድር የሚ​ደ​ረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃ​ጥ​ኣን የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸው ጻድ​ቃን አሉ፥ ለጻ​ድ​ቃ​ንም የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ላ​ቸው ኃጥ​ኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።


የሕ​ያ​ዋን ሁሉ ነፍስ፥ የሰ​ውም ሁሉ መን​ፈስ በእጁ ናትና።


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሁሉን ሰጥ​ተ​ኸ​ና​ልና ሰላ​ምን ስጠን።


ኃጥኣን ግን በክፉ ቀን ይጠፋሉ።


ኀጢ​አ​ቴን ነገ​ርሁ፤ በደ​ሌ​ንም አል​ሸ​ሸ​ግ​ሁም፤ ስለ ኀጢ​አቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሴን እከ​ስ​ሳ​ለሁ አልሁ፤ አን​ተም የል​ቤን ሽን​ገላ ተው​ልኝ።


ለሚ​ጸ​ልይ ጸሎ​ቱን ይሰ​ጠ​ዋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ንን ዘመን ይባ​ር​ካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይ​ደ​ለ​ምና።


ሰነፍ ነገ​ርን ያበ​ዛል፤ ሰውም የሆ​ነ​ው​ንና ወደ ፊት የሚ​ሆ​ነ​ውን አያ​ው​ቅም፤ ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?


ጥበ​ብን አውቅ ዘንድ በም​ድር የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ድካም አይ ዘንድ ልቤን ሰጠሁ፥ በቀ​ንና በሌ​ሊት እን​ቅ​ል​ፍን በዐ​ይኑ የሚ​ያይ የለ​ምና።


አው​ቅና እመ​ረ​ምር ዘንድ ጥበ​ብ​ንና የነ​ገ​ሩን ሁሉ መደ​ም​ደ​ሚያ እፈ​ልግ ዘንድ፥ የክ​ፉ​ዎ​ች​ንም ስን​ፍ​ናና ዕብ​ደት አውቅ ዘንድ እኔ በልቤ ዞርሁ።


ጻድቅ በጽ​ድቁ ሲጠፋ፥ ኃጥ​እም በክ​ፋቱ ሲኖር፥ ይህን ሁሉ በከ​ንቱ ዘመኔ አየሁ።


ልቤም ብዙ ጥበ​ብ​ንና አእ​ም​ሮን፥ ምሳ​ሌ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ተመ​ለ​ከ​ተች። ይህም ነፋ​ስን መከ​ተል እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።


ጠላት በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁል​ጊዜ በት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ላይ እጅ​ህን አንሣ።


“እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እለ​ም​ነው ነበር፥ የሁሉ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጠ​ራው ነበር።


ፍቅ​ራ​ቸ​ውና ጥላ​ቸው ቅን​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ን​ድ​ነት እነሆ፥ ጠፍ​ቶ​አል፤ ከፀ​ሓይ በታ​ችም በሚ​ሠ​ራው ነገር ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዕድል ፈንታ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የላ​ቸ​ውም።


ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንም፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከሳ​ፋን ልጅ ከአ​ኪ​ቃም ልጅ ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የተ​ዋ​ቸ​ውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስ​ንና የኔ​ር​ዩን ልጅ ባሮ​ክ​ንም ወሰዱ።


እነሆ፥ ሁላ​ች​ሁም፥ በክ​ፉ​ዎች ላይ ክፋት እን​ደ​ም​ት​መ​ጣ​ባ​ቸው ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም ምንም የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ እን​ዴ​ትስ እን​ደ​ሚ​ሆን የሚ​ነ​ግ​ረው ማን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios