አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስጡ፤ ለዘለዓለምም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣውንም ከእናንተ እንዲመልስ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተገዙ።
ዘዳግም 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነህና አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ ዛሬ ዕወቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሣ አለመሆኑን አስተውል፤ አንተ ዐንገተ ደንዳና ነህና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አንተ ልበ ደንዳና ሕዝብ ነህና ጌታ አምላክህ ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳልሆነ እወቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ አንተ ልብህ የደነደነ እልኸኛ ስለ ሆንክ እግዚአብሔር ይህችን ለም ምድር የሚሰጥህ አንተ እርስዋን ለመውረስ የተገባህ አለመሆንህን ዕወቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነህና አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ እወቅ። |
አሁንም እንደ አባቶቻችሁ አንገታችሁን አታደንድኑ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ስጡ፤ ለዘለዓለምም ወደ ተቀደሰው ወደ መቅደሱ ግቡ፤ ጽኑ ቍጣውንም ከእናንተ እንዲመልስ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ተገዙ።
ደግሞም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ።
ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ምድር አስገባሃለሁ፤ አንገተ ደንዳና ስለሆኑ ሕዝብህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ ከአንተ ጋር አልወጣም።”
“አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማማነታችንን፥ ኀጢአታችንንና በደላችንን ይቅር በለን፤ ለአንተም እንሆናለን” አለ።
እነርሱ ፊታቸው የከፋ፥ ልባቸው የደነደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፤ አንተም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው።
የእስራኤል ቤት ሆይ! እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ርኩስ ሥራችሁ ሳይሆን ስለ ስሜ ስል በሠራሁላችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ! በገባችሁባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ የምሠራ አይደለሁም።
“እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ።
“በዚያም ዘመን እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ መሣሪያችሁን ይዛችሁ እናንተ አርበኞች ሁሉ በወንድሞቻችሁ በእስራኤል ልጆች ፊት ትሻገራላችሁ።
እኔ ዐመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፤ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፃችኋል፤ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?
እግዚአብሔርም አለኝ፦ ‘አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም እንዲህ ብዬ ነገርሁህ፤ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና ሕዝብ እንደ ሆነ አይችአለሁ፤