La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 9:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ውጡ፤ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁ​ንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ካ​ችሁ ጊዜ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዐመ​ፃ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም አላ​መ​ና​ች​ሁም፤ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ከቃዴስ በርኔ ባስወጣችሁ ጊዜ፣ “ውጡ፤ የሰጠኋችሁንም ምድር ርስት አድርጋችሁ ውረሷት” አላችሁ። እናንተ ግን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፤ እርሱን አልታመናችሁበትም፤ አልታዘዛችሁትምም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም፥ ‘ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ፥ በጌታ በአምላካችሁ ቃል ላይ ዐመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፥ ለቃሉም አልታዛችሁም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር፥ ‘ሂዱ፤ የሰጠኋችሁንም የተስፋ ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁም ጊዜ በእርሱ ላይ ዐመፃችሁ እንጂ አልተማመናችሁበትም፤ ለቃሉም አልታዘዛችሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም፦ ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ቃል ዐመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፥ ድምፁንም አልሰማችሁም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 9:23
13 Referencias Cruzadas  

እነ​ርሱ ግን ዐመ​ፁ​በት፤ ቅዱስ መን​ፈ​ሱ​ንም አስ​መ​ረሩ፤ ስለ​ዚህ ተመ​ልሶ ጠላት ሆና​ቸው፤ እር​ሱም ተዋ​ጋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ፥ “በዚህ ምድረ በዳ ከም​ን​ሞት በግ​ብፅ ምድር ሳለን ብን​ሞት በተ​ሻ​ለን ነበር።


ነገር ግን እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አታ​ምፁ፤ እኛ እና​ጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ንና የም​ድ​ሪ​ቱን ሰዎች አት​ፍሩ፤ ጊዜ​አ​ቸው አል​ፎ​ባ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኛ ጋር ነው፤ አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው” ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው።


በሴ​ይር ተራራ መን​ገድ ከኮ​ሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የዐ​ሥራ አንድ ቀን ጕዞ ነው።


እር​ሱም አለ፦ ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ በመ​ጨ​ረ​ሻው ዘመን ምን እንደ ሆነ አያ​ለሁ፤ ጠማማ ትው​ልድ፥ እም​ነት የሌ​ላ​ቸው ልጆች ናቸ​ውና።


ለእ​ነ​ዚያ ደግሞ እንደ ተነ​ገረ ለእ​ኛም የም​ሥ​ራች ተሰ​ብ​ኮ​ል​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ሙት ቃል ከሰ​ሚ​ዎቹ ጋር በእ​ም​ነት ስላ​ል​ተ​ዋ​ሐደ አል​ጠ​ቀ​ማ​ቸ​ውም።