ዘዳግም 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፤ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና መገበህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው በእያንዳንዱ ቃል እንጂ፣ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ሊያስተምርህ አስራበህ፤ አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቁትን መና መገበህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከጌታ አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ሊያሳውቅህ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በራብ እንድትሠቃይ አደረገህ፤ ቀጥሎም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ የማታውቁትን መና አበላህ፤ ይህንንም ማድረጉ ሰው ሕይወቱ ተጠብቆለት መኖር የሚችለው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አለመሆኑን ሊያስተምርህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ። |
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ነው እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም የሚል ተጽፎአል” አለው።
አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ እንጀራ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክረውን መጠጥም አልጠጣችሁም።
ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ አይደለምና፤ በዚህም ነገር ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር ዘመናችሁ ይረዝማል።”
ሁለቱን የድንጋይ ጽላት፥ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የተማማለባቸውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀበል ዘንድ ወደ ተራራ በወጣሁ ጊዜ፥ በተራራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀምጬ ነበር፤ እንጀራ አልበላሁም፤ ውኃም አልጠጣሁም።