ዘዳግም 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከበላህና ከጠገብህ በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህባት በኋላ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለዚያ በልተህ ስትጠግብና ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ መኖር ስትጀምር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልተህ በምትጠግብበት፥ መልካምም ቤት ሠርተህ በምትኖርበት ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በልተህ በምትጠግብበትና ጥሩ ቤቶች ሠርተህ በምትኖርበት ጊዜ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከበላህና ከጠገብህ በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህበት በኋላ፥ |
ድሃውንም ደብድባችኋልና፤ መማለጃንም ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
ለአባቶቻቸው ወደ ማልሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ምድር ካገባኋቸው በኋላ፥ ከበሉም፥ ከጠገቡም በኋላ ይስታሉ፤ ሌሎችን አማልክትም ወደ ማምለክ ይመለሳሉ፤ እኔንም ያስቈጡኛል፤ ቃል ኪዳኔንም ያፈርሳሉ።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
“አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ባገባህ ጊዜ፤ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥