ዘዳግም 33:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ጋር በተሰበሰቡ ጊዜ፥ አለቃ በተወዳጁ ዘንድ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋራ ሆነው፣ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣ እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፥ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፥ እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ነገዶችና የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ነገሠ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች 2 ሁሉ ጋር በተከማቹ ጊዜ፥ 2 ንጉሥ በይሹሩን ነበረ። |
ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፤ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ” አለው።
አሁንም እመክርሃለሁና ስማኝ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፤ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤
የፈጠረህ ከማኅፀንም የሠራህ የሚረዳህም እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፥ “ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ወዳጄ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ።
በያዕቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእስራኤልም ሕማም አይታይም፤ አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው፤ የአለቆችም ክብር ለእርሱ ነው።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
“ለሰቂማ ሰዎች ሁሉ፦ ሰባ የሆኑት የይሩበኣል ልጆች ሁሉ ቢገዙአችሁ ወይስ አንድ ሰው ቢገዛችሁ ምን ይሻላችኋል? ብላችሁ ንገሩአቸው፤ ደግሞም እኔ የአጥንታችሁ ፍላጭ፥ የሥጋችሁ ቍራጭ እንደ ሆንሁ አስቡ።”