Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 33:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋራ ሆነው፣ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣ እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፥ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፥ እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የእስራኤል ነገዶችና የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ነገሠ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ሁሉ ጋር በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ፥ አለቃ በተ​ወ​ዳጁ ዘንድ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች 2 ሁሉ ጋር በተከማቹ ጊዜ፥ 2 ንጉሥ በይሹሩን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 33:5
12 Referencias Cruzadas  

በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦


“እግዚአብሔር፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”


ክርክር በኖራቸው ቍጥር ጕዳያቸው ወደ እኔ ይመጣል፤ ለግራና ለቀኙ የሚሆነውን እኔ ወስኜ የእግዚአብሔርን ሥርዐትና ሕጎች እነግራቸዋለሁ።”


ምክር እሰጥሃለሁና አሁን እኔን ስሙኝ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሁን። አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝብን የምትወክል መሆን አለብህ፤ ክርክራቸውን ወደ እርሱ ታቀርባለህ።


የፈጠረህ፣ በማሕፀን የሠራህ፣ የሚረዳህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህ ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ።


“በያዕቆብ መጥፎ ነገር አልተገኘም፤ በእስራኤልም ጕስቍልና አልታየም፤ እግዚአብሔር አምላኩ ከርሱ ጋራ ነው፤ የንጉሡም እልልታ በመካከላቸው ነው።


ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ።


“አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ፣ በደመናትም ላይ በግርማው እንደሚገሠግሥ፣ እንደ ይሹሩን አምላክ ያለ ማንም የለም።


በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ እያንዳንዱም ሰው መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ነበር።


እስራኤላውያንም ጌዴዎንን፣ “ከምድያማውያን እጅ ታድገኸናልና አንተ፣ ልጅህና የልጅ ልጅህ ግዙን” አሉት።


“የሴኬምን ነዋሪዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፤ ‘ሰባዎቹ የይሩባኣል ልጆች ቢገዟችሁ ይሻላል ወይስ አንድ ሰው ብቻ?’ የሥጋችሁ ቍራጭ፣ የዐጥንታችሁ ፍላጭ መሆኔን ልብ በሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos