ዘዳግም 32:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔ ዘንድ ያለው ትእዛዝ ይህ አይደለምን? በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ይህስ በእኔ ዘንድ የተጠበቀ፥ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ የለምን? 2 በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን? |
“እናንተና አባቶቻችሁ፥ ነገሥታቶቻችሁም፥ አለቆቻችሁም የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው፥ በልቡም ያኖረው አይደለምን?
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።
ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
ዛሬም እንዳሉ እግዚአብሔር በቍጣና በመቅሠፍት፥ በታላቅም መዓት ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው።