ዘዳግም 3:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፥ አንተም የምታያትን ምድር እርሱ ያወርሳቸዋልና ኢያሱን እዘዘው፤ አደፋፍረውም፥ አጽናውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሕዝቡን መርቶ በማሻገር የምታያትን ምድር እንዲወርሱ የሚያደርጋቸው ስለ ሆነ፣ ኢያሱን ላከው፤ አደፋፍረው፤ አበረታታውም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቅስ ኢያሱን እዘዘው፥ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፥ አንተም የምታያትን ምድር እርሱ ያወርሳቸዋልና፥ አደፋፍረውም፥ አበርታውም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቅስ ለኢያሱ አስፈላጊውን መመሪያ ስጠው፤ በማበረታታትም አጠንክረው፤ ሕዝቡ ተሻግረው ይህችን የምታያትን ምድር ይወርሱ ዘንድ የሚመራቸው እርሱ ነው።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፥ አንተም የምታያትን ምድር እርሱ ያወርሳቸዋልና ኢያሱን እዘዘው፥ አደፋፍረውም፥ አጽናውም። |
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን፥ “ጠንክር፤ ሰው ሁን፤ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነውን ሥራ ሁሉ እስክትፈጽም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአደባባዩ፥ የቤተ መዛግብቱ፥ የሰገነቱ፥ የውስጡ ቤተ መዛግብት፥ የስርየት ቤቱና፥ የእግዚአብሔር ቤት ምሳሌ።
ኢያሱና አባቶቻችንም በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ፊት አስወጥቶ ወደ ሰደዳቸው ወደ አሕዛብ ሀገር ከእነርሱ ጋር አገቡአት፤ እስከ ዳዊት ዘመንም ነበረች።
የነዌንም ልጅ ኢያሱን፥ “የእስራኤልን ልጆች እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ወደ ማለላቸው ምድር ታገባለህና ጽና፤ በርታ፤ እርሱም ከአንተ ጋር ይሆናል” ብሎ አዘዘው።
አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ በፊትህ ያልፋል፤ እርሱ እነዚህን አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ ትወርሳቸውማለህ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ኢያሱ በፊትህ ይሄዳል።
ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት፦ ‘አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋር እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው እንዲሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ትገባለህና፥ እርስዋንም ለእነርሱ ታወርሳለህና ጽና፤ በርታ።
“አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል፤ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስን ተሻገሩ።