“አባቶቻችን በእርስዋ የተጻፈውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚህችን መጽሐፍ ቃል ስላልሰሙ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁዳም ሁሉ ስለዚችም ስለተገኘችው መጽሐፍ ቃል ሁሉ እግዚአብሔርን ጠይቁ።
ዘዳግም 27:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የዚህን ሕግ ቃሎች ያደርግ ዘንድ የማያጸና ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “‘የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘እነዚህን የእግዚአብሔርን ሕግ ቃላት ሁሉ የማይፈጽም ሁሉ የተረገመ ይሁን።’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን’ ይበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚህን ሕግ ቃሎች ያደርግ ዘንድ የማያጸና ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይላሉ። |
“አባቶቻችን በእርስዋ የተጻፈውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚህችን መጽሐፍ ቃል ስላልሰሙ በላያችን የነደደ የእግዚአብሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁዳም ሁሉ ስለዚችም ስለተገኘችው መጽሐፍ ቃል ሁሉ እግዚአብሔርን ጠይቁ።
የአምላክህንም ሕግ፥ የንጉሡንም ሕግ በማያደርግ ሁሉ ላይ ሞት፥ ወይም ስደት፥ ወይም ገንዘብ መወረስ፥ ወይም ግዞት በፍጥነት ይፈረድበት።”
ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ ኀጢአትንም ቢሠራ፥ ኀጢአተኛውም እንደሚያደርገው ርኵሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ በአደረገው ዐመፅና በሠራት ኀጢአት በዚያች ይሞታል።
በኦሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእርግማን ውስጥ ይኖራሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በዚህ በኦሪት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ሁሉ የማይፈጽምና የማይጠብቅ ርጉም ይሁን።”
“በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን፥ የተቀረፀ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።