በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፤ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባችሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”
ዘዳግም 26:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዐሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የምድርህን ፍሬ ሁሉ ዐሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ ሁለተኛ ዐሥራት አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ ይበሉ ዘንድ፥ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛውም፥ ለድሃ-አደጉም፥ ለመበለቲቱም ስጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዐሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ምርት አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፣ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሥራት በምታወጣት በሦስተኛው ዓመት ከምርትህ አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሦስተኛው ዓመት ማለት ዐሥራት በምታወጣት ዓመት ዐሥራትህን ሁሉ አጠናቅቀህ ከሰበሰብክ በኋላ በከተማህ ለሚገኙ ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥተህ ጠግበው እንዲበሉ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የፍሬህን ሁሉ አሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ በአገርህ ደጅ ውስጥ ይበሉ ዘንድ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድሀ አደጉም ለመበለቲቱም ስጣቸው። |
በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፤ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባችሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”
ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዖን እንዲሆን በግብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደረጋት።
“የምድርም ዐሥራት፥ ወይም የምድር ዘር፥ ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።
ለእግዚአብሔር መባ አድርገው የሚለዩትን የእስራኤልን ልጆች ዐሥራት ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፤ ስለዚህ፦ በእስራኤል ልጆች መካከል ርስት አትወርሱም አልኋቸው።”
አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሃ-አደግና መበለትም በበዓልህ ደስ ይበላችሁ።
ከሌዊ ልጆችም፥ ክህነትን የሚቀበሉት ከሕዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ ከእነርሱ ዐሥራትን በሕግ እንዲያስወጡ ትእዛዝ አላቸው።