ዘዳግም 25:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እህልህን በምታበራይ ጊዜ በሬዉን አፉን አትሰረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እህል በምታበራይበት ጊዜ የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እህል የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር። |
ጥቍሩን አዝሙድ በተሳለች ማሄጃ አያሄድም፤ የሰረገላም መንኰራኵር በከሙን ላይ አይዞርም፤ ነገር ግን ጥቍሩን አዝሙድ በሽመል፥ ከሙኑንም በበትር ይወቃል።
ኤፍሬምም ቀንበርን እንደ ለመደች ጊደር ነው፤ እኔ ግን በአንገቱ ውበት እጫንበታለሁ፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፤ ይሁዳንም እለጕመዋለሁ፤ ያዕቆብም ለራሱ መንግሥትን ያስተካክላል።