Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 28:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ጥቍ​ሩን አዝ​ሙድ በተ​ሳ​ለች ማሄጃ አያ​ሄ​ድም፤ የሰ​ረ​ገ​ላም መን​ኰ​ራ​ኵር በከ​ሙን ላይ አይ​ዞ​ርም፤ ነገር ግን ጥቍ​ሩን አዝ​ሙድ በሽ​መል፥ ከሙ​ኑ​ንም በበ​ትር ይወ​ቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ጥቍር አዝሙድ በመውቂያ መሣሪያ አይወቃም፤ ከሙን የሠረገላ መንኰራኵር አይሄድበትም፤ ጥቍር አዝሙድ በበትር፣ ከሙንም በዘንግ ይወቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ጥቁሩ አዝሙድ በመውቂያ አይወቃም፥ ከሙንም የሠረገላ መንኰራኵር አይዞርበትም፤ ነገር ግን ጥቁሩ አዝሙድ በሽመል ከሙኑም በበትር ይወቃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ጥቊር አዝሙድን፥ ከሙንን በብረት መውቂያ በሠረገላ መንኰራኲር አይወቃም፤ ከዚህ ይልቅ መጠነኛ ክብደት ባለው በትር ይወቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ጥቁሩ አዝሙድ በተሳለች ማሄጃ አያኬድም፥ የሰረገላም መንኮራኵር በካሙን ላይ አይዞርም፥ ነገር ግን ጥቁሩ አዝሙድ በሽመል ከሙኑም በበትር ይወቃል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 28:27
10 Referencias Cruzadas  

ለኢ​ዮ​አ​ካ​ዝም ከኀ​ምሳ ፈረ​ሰ​ኞች፥ ከዐ​ሥ​ርም ሰረ​ገ​ሎች፥ ከዐ​ሥር ሺህም እግ​ረ​ኞች በቀር ሕዝብ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም፤ የሶ​ርያ ንጉሥ አጥ​ፍ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ በአ​ው​ድ​ማም እን​ዳለ ዕብቅ አድ​ቅ​ቆ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


ብልህ ንጉሥ የኃጥኣን መንሽ ነው፥ በእነርሱ ላይም መንኰራኵርን ይነዳባቸዋል።


ምድ​ርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ ተምራ ደስ ይላ​ታል።


እኔ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ና​ንተ ላይ አል​ቈ​ጣም፤ የም​ሕ​ረ​ቴም ድምፅ አያ​ጠ​ፋ​ች​ሁም።


እነሆ፥ እንደ ተሳ​ለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ታሄ​ዳ​ለህ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ታደ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ እንደ ገለ​ባም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።


አቤቱ! ቅጣን፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ እን​ዳ​ታ​ጠ​ፋን በፍ​ር​ድህ ይሁን እንጂ በቍ​ጣህ አይ​ሁን።


አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም ያሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለ​ሁና፥ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ያለ ቅጣ​ትም አል​ተ​ው​ህም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች በብ​ረት መጋዝ ሰን​ጥ​ቀ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የደ​ማ​ስቆ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos