ዘዳግም 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳነህ ዐስብ፤ ስለዚህ ይህን ነገር ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርህና አምላክህ እግዚአብሔር ከዚያ እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ይህን እንድታደርግ ያዘዝሁህ ለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህና ጌታ እግዚአብሔር ከዚያ እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ ይህን ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም በግብጽ ባርያዎች እንደ ነበራችሁና አምላካችሁ እግዚአብሔር ነጻ እንዳወጣችሁ አስታውሱ፤ እኔም ይህን ትእዛዝ የምሰጣችሁ በዚህ ምክንያት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳነህ አስብ፤ ስለዚህ ይህን ነገር ታደርግ ዘንድ አዝዤሃለሁ። |
አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበርህ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ከዚያ እንዳዳነህ ዐስብ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝዝሃለሁ።
“የመጻተኛውንና የድሃ-አደጉን፥ የመበለቲቱንም ፍርድ አታጣምምባቸው፤ የመበለቲቱንም ልብስ ለመያዣ አትውሰድባት።
“የእርሻህን መከር ባጨድህ ጊዜ ነዶም ረስተህ በእርሻህ ብታስቀር፥ ትወስደው ዘንድ አትመለስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ፥ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ተወው።
አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፤ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ዕለተ ሰንበትን ትጠብቃትና ትቀድሳት ዘንድ አዘዘህ።