Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 24:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “የእ​ር​ሻ​ህን መከር ባጨ​ድህ ጊዜ ነዶም ረስ​ተህ በእ​ር​ሻህ ብታ​ስ​ቀር፥ ትወ​ስ​ደው ዘንድ አት​መ​ለስ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ባ​ር​ክህ፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ተወው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፣ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፣ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 “የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፥ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “እህልህን በምትሰበስብበት ጊዜ የረሳኸው ነዶ ቢኖር እርሱን ለማምጣት ወደ ኋላ አትመለስ፤ እርሱ ለመጻተኞች፥ ወላጆቻቸው ለሞቱባቸው ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው መበለቶች ይቅርላቸው፤ ይህን ብታደርግ በምትሠራው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የእርሻህን መከር ባጨድህ ጊዜ ነዶም ረስተህ በእርሻህ ብታስቀር፥ ትወስደው ዘንድ አትመለስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ፥ ለመጻተኛና ለድሃ አደግ ለመበለትም ተወው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 24:19
23 Referencias Cruzadas  

“የም​ድ​ራ​ች​ሁን መከር በሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በእ​ር​ሻ​ችሁ የቀ​ረ​ውን አጥ​ር​ታ​ችሁ አት​ጨዱ፤ የመ​ከ​ሩ​ንም ቃር​ሚያ አት​ል​ቀሙ፤ ለድ​ሆ​ችና ለእ​ን​ግ​ዶች ተዉት፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


ሌዋ​ዊ​ዉም፥ ከአ​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት የለ​ው​ምና፥ በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግም፥ መበ​ለ​ትም መጥ​ተው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤ ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ታ​ደ​ር​ገው በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ነው።


ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል።


ስጡ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ የሞ​ላና የበዛ፥ የተ​ት​ረ​ፈ​ረ​ፈም መል​ካም መስ​ፈ​ሪያ በዕ​ቅ​ፋ​ችሁ ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል፤ በሰ​ፈ​ራ​ች​ሁ​በ​ትም መስ​ፈ​ሪያ ይሰ​ፍ​ሩ​ላ​ች​ኋል።”


ጻድ​ቃን ግን ጥበ​ብን ይመ​ክ​ራሉ፤ ምክ​ራ​ቸ​ውም ትጸ​ና​ለች።


መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ተ​ኛው ይልቅ የኋ​ለ​ኛ​ውን ለኢ​ዮብ ባረከ፤ መን​ጋ​ዎ​ቹም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድ​ስት ሺህም ግመ​ሎች፥ አንድ ሺህም ጥማድ በሬ​ዎች፥ አንድ ሺህም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ።


በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ በል፦ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር ከቤቴ ለይች ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሀ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸኝ ትእ​ዛዝ ሁሉ ሰጥ​ቼ​አ​ለሁ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ምንም አላ​ፈ​ረ​ስ​ሁም፤ አል​ረ​ሳ​ሁ​ምም፤


ደግሞ ከነዶው አስቀርታችሁ ተዉላት፣ እርስዋም ትቃርም፥ አትውቀሱአትም ብሎ አዘዛቸው።


እጅ​ህን በም​ት​ጥ​ል​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ዚህ በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና ፈጽ​መህ ስጠው፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ያህል አበ​ድ​ረው፤ በሰ​ጠ​ኸ​ውም ጊዜ በል​ብህ አት​ጸ​ጸት።


አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።


ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤ ለድሃ የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።


አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ ይህን ነገር ታደ​ርግ ዘንድ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።


ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios