በምድርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸው የአሕዛብን ርኵሰት ሁሉ ያደርጉ ነበር።
ዘዳግም 23:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእስራኤል ሴቶች ልጆች ሴት አመንዝራ አትገኝ፤ ከእስራኤልም ወንዶች ልጆች ወንድ አመንዝራ አይገኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከእስራኤል ወንድ ወይም ሴት የቤተጣዖት አመንዝራ አይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላዊ የሆነ ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት የቤተ ጣዖት ተከታዮች እንደሚያደርጉት የዝሙት ሥራ አይፈጽሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤል ሴቶች ልጆች ሴት ጋለሞታ አትገኝ፥ ከእስራኤልም ወንዶች ልጆች ወንድ ጋለሞታ አይገኝ። |
በምድርም ሁሉ ዐመፅ ነበረ፥ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸው የአሕዛብን ርኵሰት ሁሉ ያደርጉ ነበር።
ሴቶቹም ለማምለኪያ ዐፀድ መጋረጃ ይፈትሉባቸው የነበሩትን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉትን የሰዶማውያንን ቤቶች አፈረሰ።
ከቀናች መንገድ እንዳያርቁህ፥ እውነትንም ከማወቅ የተለየህ እንዳያደርጉህ፤ ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ትምህርትን የምታስተው፥ ክፉ ምክር አታግኝህ፤
ወንዶችም ደግሞ ከአመንዝሮች ጋር ይጫወታሉና፥ ከጋለሞቶችም ጋር ይሠዋሉና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰሰኑ ጊዜ፥ ሙሽሮቻችሁም በአመነዘሩ ጊዜ አልቀጣኋቸውም፤ የማያስተውልም ሕዝብ ከአመንዝራ ጋር ይቀላቀላል።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
ብላቴናዪቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያውጡአት፤ በእስራኤልም ዘንድ ስንፍናን አድርጋለችና፥ የአባቷንም ቤት አስነውራለችና የከተማው ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።
ያ የደፈራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናዪቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።
ሰውነታቸውንም ደስ ባሰኙ ጊዜ የኃጥኣን ልጆች የሆኑ የከተማው ሰዎች ቤቱን ከበቡ፤ በሩንም ይደበድቡ ነበር፤ ባለቤቱንም ሽማግሌውን ሰው፥ “ወደ ቤትህ የገባውን ሰው እንድንደርስበት አውጣልን” አሉት።