ዘዳግም 22:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያ የደፈራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናዪቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ለልጅቱ አባት ዐምሳ ሰቅል ብር ይክፈል፤ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሯታልና፣ እርሷን ማግባት አለበት፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፥ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለልጃገረዲቱ አባት ኀምሳ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እርስዋም ለዚያ ሰው ሚስት ሆና ትኑር፤ አስገድዶ በመድፈር ከእርስዋ ጋር ስለ ተኛ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም። |
ከዚያም በኋላ በእርስዋ ደስ ባይልህ አርነት አውጥተህ ትለቅቃታለህ፤ በዋጋ ግን አትሸጣትም፤ አግብተሃታልና እንደባሪያ አትቍጠራት።
በእስራኤል ድንግል ላይ ክፉ ስም አምጥቶአልና መቶ የብር ሰቅል ያስከፍሉት፤ ለብላቴናዪቱም አባት ይስጡት፤ እርስዋም ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።
ብላቴናዪቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውየውም የባልጀራውን ሚስት አስነውሮአልና በድንጋይ ወግረው ይግደሉአቸው፤ እንዲሁ ክፉውን ነገር ከውስጥህ ታስወግዳለህ።