ዘዳግም 22:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናዪቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውየውም የባልጀራውን ሚስት አስነውሮአልና በድንጋይ ወግረው ይግደሉአቸው፤ እንዲሁ ክፉውን ነገር ከውስጥህ ታስወግዳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፣ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስገድዶ ስለ ደፈረ፣ ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፥ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዬውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፥ በዚህም ዓይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱንም ከከተማይቱ ወደ ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉ፤ ልጃገረዲቱ መሞት የሚገባት ሰው ሊሰማ በሚችልበት ከተማ ውስጥ እያለች ርዳታ እንዲደረግላት የጩኸት ድምፅ ባለማሰማትዋ ነው፤ ሰውየውም የሚሞትበት ምክንያት ለሌላ ሰው ከታጨች ልጃገረድ ጋር በመተኛት ሕግን በማፍረሱ ነው፤ በዚህ ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ። |
“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራዪቱ ፈጽመው ይገደሉ።
እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
ከግብፅ ምድር ካወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ካዳናችሁ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ሊያስታችሁ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ትሄድባት ዘንድ ካዘዘህ መንገድ ሊያወጣህ ተናግሮአልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገደል፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከአንተ አርቅ።
እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።
ከዚያም በኋላ በእርስዋ ደስ ባይልህ አርነት አውጥተህ ትለቅቃታለህ፤ በዋጋ ግን አትሸጣትም፤ አግብተሃታልና እንደባሪያ አትቍጠራት።
“ለወንድ የታጨች ድንግል ልጅ ብትኖር፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤
“ነገር ግን ሰው የታጨችውን ልጃገረድ በሜዳ ቢያገኛት፥ በግድ አሸንፎም ቢደርስባት፥ ያ የደረሰባት ሰው ብቻውን ይገደል።