የኢየሩሳሌምም ቅጥር በተመረቀ ጊዜ ምረቃውን በደስታና በምስጋና፥ በመዝሙርም፥ በጸናጽልም፥ በበገናም፥ በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።
ዘዳግም 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሐፍትም ለሕዝቡ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያስመርቀው ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቆቹም ለሰራዊቱ እንዲህ ይበሉ፤ “አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ አለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አለቆቹም ለሠራዊቱ እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ይሞትና ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህ በኋላ የጦር መሪዎች ለዘማቾች እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት የሠራና አስመርቆ ያልገባበት ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ሌላ ሰው ቤቱን አስመርቆ ይገባበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆችም ለሕዝቡ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ ሰው ቢኖር በሰልፍ እንዳይሞት ሌላም ሰው እንዳያስመረቀው ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። |
የኢየሩሳሌምም ቅጥር በተመረቀ ጊዜ ምረቃውን በደስታና በምስጋና፥ በመዝሙርም፥ በጸናጽልም፥ በበገናም፥ በመሰንቆም ለማድረግ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸው ዘንድ ሌዋውያኑን በየስፍራቸው ሁሉ ፈለጉ።
ከእናንተም ጥበበኞችና ዐዋቂዎች፥ አስተዋዮችም የሆኑትን ሰዎች ወሰድሁ፤ በእናንተም ላይ አለቆች፥ የሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የአምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም፥ ለፈራጆቻችሁም ጻፎች አድርጌ ሰየምኋቸው።
“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በሀገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና መባውን የሚጽፉትን ሹሙ፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድን ይፍረዱ።
ወይንም ተክሎ ደስ ያልተሰኘበት ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው ደስ እንዳይሰኝበት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።