የተመሸጉትንም ከተሞች ሁሉ ትመታላችሁ፤ የሚያምሩትንም ዛፎች ሁሉ ትቈርጣላችሁ፤ የውኃውንም ምንጮች ሁሉ ትደፍናላችሁ፤ መልካሞቹንም እርሻዎች ሁሉ በድንጋይ ታበላሻላችሁ።”
ዘዳግም 20:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፤ ትቈርጣቸውማለህ፤ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚበላ ፍሬ እንደማያፈራ የምታውቀውን ዛፍ ግን ልትቈርጠውና ጦርነት የምታካሂድባትን ከተማ በድል እስክትቈጣጠራት ድረስ ለከበባው ምሽግ መሥሪያ ልትጠቀምበት ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፥ ትቆርጣቸዋለህ፥ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍሬ የማያፈሩትን ሌሎች ዛፎች ግን እየቈረጥህ በመከመር ከተማይቱ እስከምትማረክበት ጊዜ ድረስ ለከበባ ተግባር ልትጠቀምባቸው ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለመብል የማይሆኑትን የምታውቃቸውን ዛፎች ታጠፋቸዋለህ፥ ትቈርጣቸውማለህ፤ እስክታሸንፋትም ድረስ በምትዋጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመሽጋለህ። |
የተመሸጉትንም ከተሞች ሁሉ ትመታላችሁ፤ የሚያምሩትንም ዛፎች ሁሉ ትቈርጣላችሁ፤ የውኃውንም ምንጮች ሁሉ ትደፍናላችሁ፤ መልካሞቹንም እርሻዎች ሁሉ በድንጋይ ታበላሻላችሁ።”
በኢየሩሳሌምም በብልሃተኞች እጅ የተሠሩትን ፥ በግንብና በቅጥር ላይ የሚኖሩትን፥ ፍላጻና መርግ የሚወረወርባቸውን መሣሪያዎች አደረገ፤ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በድንቅ ረድቶታልና የመሣሪያዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።
ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፤ ፍላጻንም አይወረውርባትም፤ በጋሻም አይመጣባትም፥ አያጥራትምም።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለምሽግና ለመከላከያ ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦
ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ኀይልን አፍስሱ ይህች ከተማ የሐሰት ከተማ ናት፤ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።
ብዙዎችን ነፍሳት ለማስወገድ ምሽግን በመሸጉ፥ ቅጥርንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈርዖን በታላቅ ኀይልና በብዙ ሕዝብ በጦርነት አይረዳውም።
ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ታላቅና ብዙ ነው፤ ከእኛም ይጠነክራሉ፤ ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሸጉም፥ እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፤ የረዐይትንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት።’
“ከተማዪቱን ለመውጋትና ለመውሰድ ብዙ ቀን ብትከብባት፥ ምሳርህን አንሥተህ ዛፎችዋን አትቍረጥ፤ ከእነርሱ ትበላለህና አትቍረጣቸው፤ ወደ አንተ ይመጣና ወደ ቅጥርህም ይገባ ዘንድ የምድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን?