Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 “ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለመ​ው​ጋ​ትና ለመ​ው​ሰድ ብዙ ቀን ብት​ከ​ብ​ባት፥ ምሳ​ር​ህን አን​ሥ​ተህ ዛፎ​ች​ዋን አት​ቍ​ረጥ፤ ከእ​ነ​ርሱ ትበ​ላ​ለ​ህና አት​ቍ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ አንተ ይመ​ጣና ወደ ቅጥ​ር​ህም ይገባ ዘንድ የም​ድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፣ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቍረጣቸው፤ ከብበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 “አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቁረጣቸው፤ ከበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “አንዲት ከተማ ለመማረክ በምትዘጋጅበት ጊዜ ከበባው ረጅም ጊዜ የወሰደ እንደ ሆነ የዛፎቹ ፍሬ ምግብ ሊሆኑህ ስለሚችሉና ዛፎችም እንደ ሰዎች ከበባ የሚደረግባቸው ስላልሆኑ ዛፎችን አትቊረጥ። የሜዳ ዛፎችን ከበባ የምታደርግባቸው ሰዎች ናቸውን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከተማይቱን ለመውሰድ በመውጋት ብዙ ቀን ከብበህ ባስጨነቅሃት ጊዜ፥ ምሳርህን አንሥተህ ዛፎችዋን አትቁረጥ፤ ከእነርሱ ትበላለህና አትቁረጣቸው፤ ከብበህ የምታጠፋው የምድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን?

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 20:19
11 Referencias Cruzadas  

የተ​መ​ሸ​ጉ​ት​ንም ከተ​ሞች ሁሉ ትመ​ታ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ት​ንም ዛፎች ሁሉ ትቈ​ር​ጣ​ላ​ችሁ፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ትደ​ፍ​ና​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ሞ​ቹ​ንም እር​ሻ​ዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ታበ​ላ​ሻ​ላ​ችሁ።”


ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሱ፤ በመ​ል​ካ​ሞ​ቹም እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ እስ​ኪ​ሞሉ ድረስ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው አንድ አንድ ድን​ጋይ ይጥል ነበር፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወን​ጭ​ፎ​ችም ከብ​በው መቱ​አ​ቸው።


ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ዛፎ​ች​ዋን ቍረጡ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ኀይ​ልን አፍ​ስሱ ይህች ከተማ የሐ​ሰት ከተማ ናት፤ መካ​ከ​ልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና “ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ፤” አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።


አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቍኦረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።


ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው ያደ​ረ​ጉ​ትን ርኵ​ሰት ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​አ​ችሁ፥ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ሠሩ ትረ​ግ​ማ​ቸ​ዋ​ለህ።


ለመ​ብል የማ​ይ​ሆ​ኑ​ትን የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ዛፎች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ትቈ​ር​ጣ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እስ​ክ​ታ​ሸ​ን​ፋ​ትም ድረስ በም​ት​ዋ​ጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመ​ሽ​ጋ​ለህ።


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ክፉ ነገር አደ​ረ​ጉ​ብን፤ አስ​ጨ​ነ​ቁ​ንም፤ በላ​ያ​ች​ንም ከባድ ሥራን ጫኑ​ብን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos