አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለበዓል መሠዊያን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ አመለካቸውም።
ዘዳግም 20:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአማልክቶቻቸው ያደረጉትን ርኵሰት ሁሉ ታደርጉ ዘንድ እንዳያስተምሩአችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት እንዳትሠሩ ትረግማቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩሃል፤ በአምላክህ በእግዚአብሔርም ላይ ኀጢአት ትሠራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ትሠራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የምታደርጉት ለባዕዳን አማልክቶቻቸው ስለ መስገድ አጸያፊ የሆነውን ነገር ሁሉ ለእናንተ በማስተማር እግዚአብሔር የሚጠላውን ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጉአችሁ ነው። |
አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለበዓል መሠዊያን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ አመለካቸውም።
እኔን እንድትበድል እንዳያደርጉህ በሀገርህ ላይ አይቀመጡ፤ አማልክቶቻቸውንም ብታመልክ ወጥመድ ይሆኑብሃልና።”
በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤
ሴቶች ልጆቻቸውምንም ከወንድ ልጆችህ፥ ሴቶች ልጆችህንም ከወንድ ልጆቻቸው ጋር እንዳታጋባ፥ ልጆቻቸውም አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ከአምላኮቻቸው በኋላ ሄደው አመንዝረውም ልጆችህን እንዳያስቱ ተጠንቀቅ።
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።
“አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት ታደርግ ዘንድ አትማር።
ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር እንዳዘዘህ ኬጤዎናዊዉን፥ አሞሬዎናዊዉን፥ ከነዓናዊዉንም፥ ፌርዜዎናዊዉንም፥ ኤዌዎናዊዉንም፥ ኢያቡሴዎናዊዉንም፥ ጌርጌሴዎናዊዉንም ፈጽመህ ትረግማቸዋለህ።
“ከተማዪቱን ለመውጋትና ለመውሰድ ብዙ ቀን ብትከብባት፥ ምሳርህን አንሥተህ ዛፎችዋን አትቍረጥ፤ ከእነርሱ ትበላለህና አትቍረጣቸው፤ ወደ አንተ ይመጣና ወደ ቅጥርህም ይገባ ዘንድ የምድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን?
ምድራቸውን ትወርሳት ዘንድ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኀጢአት ምክንያትና ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ መውደቂያና ወጥመድ፥ በእግራችሁም ችንካር፥ በዐይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንዳያጠፋቸው ራሳችሁ ዕወቁ።
ስለዚህም እኔ አሕዛብን ከፊታችሁ አላወጣቸውም፤ ነገር ግን ያስጨንቋችኋል፤ አማልክቶቻቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል” አልሁ።