La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሰ​ላም ቃልም ቢመ​ል​ሱ​ልህ ደጅም ቢከ​ፍ​ቱ​ልህ፥ በከ​ተ​ማው ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገ​ብ​ሩ​ልህ፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ይሁ​ኑህ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የቅጽር በሮቻቸውን ከፍተው እንዲገብሩ የሰላም ድርድርህን ቢቀበሉ በከባድ ሥራ ያገልግሉህ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዕርቅ ቃልም ቢመልሱልህ ደጅም ቢከፍቱልህ፥ በከተማ ውስጥ ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገብሩልህ ያገልግሉህም።

Ver Capítulo



ዘዳግም 20:11
16 Referencias Cruzadas  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በዘ​መኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎ​ሞን በአ​ባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመ​ሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ወደ ሰሎ​ሞን ላከ።


እር​ሱም፥ “በሰ​ይ​ፍ​ህና በቀ​ስ​ትህ የማ​ረ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ግደል እንጂ በሰ​ይ​ፍ​ህና በቀ​ስ​ትህ የማ​ረ​ክ​ሃ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምና አት​ግ​ደ​ላ​ቸው። ይል​ቁ​ንስ እን​ጀ​ራና ውኃ በፊ​ታ​ቸው አቅ​ር​ብ​ላ​ቸው፤ በል​ተ​ውና ጠጥ​ተ​ውም ወደ ጌታ​ቸው ይመ​ለሱ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከክፉ ሁሉ ይጠ​ብ​ቅህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነፍ​ስ​ህ​ንም ይጠ​ብ​ቃት።


የሀ​ገሩ ሰዎች ግን ይጠ​ሉት ነበ​ርና፥ ይህ በእኛ ላይ ሊነ​ግሥ አን​ሻም ብለው አከ​ታ​ት​ለው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ።


“ለመ​ዋ​ጋት ወደ አን​ዲት ከተማ በደ​ረ​ስህ ጊዜ አስ​ቀ​ድ​መህ በሰ​ላም ቃል ጥራ​ቸው።


የሰ​ላም ቃልም ባይ​መ​ል​ሱ​ልህ ከአ​ን​ተም ጋር መዋ​ጋት ቢወ​ድዱ፥ አንተ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ትከ​ብ​ባ​ለህ፤


በጋ​ዜ​ርም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ኤፍ​ሬም አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በኤ​ፍ​ሬም መካ​ከል ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ገባ​ርም ሆኑ።


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


ኢያ​ሱ​ንም፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገ​ርም ነን” አሉት። ኢያ​ሱም፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ? ከወ​ዴ​ትስ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው።


እነ​ር​ሱም አሉት፥ “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪ​ያ​ዎ​ችህ መጥ​ተ​ናል፤ ዝና​ው​ንም፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥


እስ​ራ​ኤ​ልም በበ​ረቱ ጊዜ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ገባ​ሮች አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፏ​ቸ​ውም።