La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለመ​ዋ​ጋት ወደ አን​ዲት ከተማ በደ​ረ​ስህ ጊዜ አስ​ቀ​ድ​መህ በሰ​ላም ቃል ጥራ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፣ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፥ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“በአንዲት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል በምትዘምትበት ጊዜ በመጀመሪያ እንዲገብሩ የሰላም ድርድር ጠይቅ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለመዋጋት ወደ አንዲት ከተማ በደረስህ ጊዜ አስቀድመህ በዕርቅ ቃል ጥራቸው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 20:10
13 Referencias Cruzadas  

በሩ​ቅም በቅ​ር​ብም ላሉ በሰ​ላም ላይ ሰላም ይሁን፤ እፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሰረገላውንም ከኤፍሬም ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፣ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።


ቃሉን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላከ፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምን ነገ​ራ​ቸው፤ እር​ሱም የሁሉ ገዢ ነው።


ነገር ግን ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ከራሱ ጋር ከአ​ስ​ታ​ረ​ቀን፥ የማ​ስ​ታ​ረቅ መል​እ​ክ​ት​ንም ከሰ​ጠን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።


መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን።


“ከቄ​ድ​ሞ​ትም ምድረ በዳ የሰ​ላ​ምን ቃል ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ወደ ሐሴ​ቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እን​ዲህ ብዬ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክሁ፦


የሰ​ላም ቃልም ቢመ​ል​ሱ​ልህ ደጅም ቢከ​ፍ​ቱ​ልህ፥ በከ​ተ​ማው ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገ​ብ​ሩ​ልህ፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ይሁ​ኑህ።


ጸሐ​ፍ​ቱም ለሕ​ዝቡ ነግ​ረው በጨ​ረሱ ጊዜ ከታ​ላ​ላቁ ሕዝብ መካ​ከል የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆ​ችን ይሹሙ።


ዮፍ​ታ​ሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ “ሀገ​ሬን ለመ​ው​ጋት ወደ እኔ የም​ት​መጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ?” ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ።


ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በሬ​ሞን ዐለት ወዳ​ሉት ወደ ብን​ያም ልጆች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ፤ በሰ​ላ​ምም ጠሩ​አ​ቸው።