Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 21:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በሬ​ሞን ዐለት ወዳ​ሉት ወደ ብን​ያም ልጆች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላኩ፤ በሰ​ላ​ምም ጠሩ​አ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም ጉባኤው በሙሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ብንያማውያን የሰላም ጥሪ አስተላለፈ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከዚያም ጉባኤው በሙሉ በሬሞን ዐለት ወዳሉት ብንያማውያን የሰላም ጥሪ አስተላለፈ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚህ በኋላ መላው ጉባኤ የሪሞን አለት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ወደነበሩት ብንያማውያን መልእክት ልከው ጦርነቱ እንዲቆም ተስማሙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ማኅበሩም ሁሉ በሬሞን ዓለት ወዳሉት ወደ ብንያም ልጆች መልክተኞችን ላኩ፥ በዕርቅ ቃልም ተናገሩአቸው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 21:13
9 Referencias Cruzadas  

በሩ​ቅም በቅ​ር​ብም ላሉ በሰ​ላም ላይ ሰላም ይሁን፤ እፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወደ ገባ​ች​ሁ​በት ቤትም አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ ‘ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላም ይሁን’ በሉ።


መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን።


“ለመ​ዋ​ጋት ወደ አን​ዲት ከተማ በደ​ረ​ስህ ጊዜ አስ​ቀ​ድ​መህ በሰ​ላም ቃል ጥራ​ቸው።


ላቦስ ሳሌ፥ ኤር​ሞ​ትም ሃያ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ረ​ፉት ተመ​ል​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በየ​መ​ን​ገዱ ላይ አም​ስት ሺህ ሰውን ለቀሙ፤ ወደ ጊድ​ዓ​ምም አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደሉ።


ስድ​ስ​ቱም መቶ ሰዎች ተመ​ል​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወደ ሬሞን ዓለት ሸሹ፤ በሬ​ሞ​ንም ዓለት አራት ወር ተቀ​መጡ።


በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ በሚ​ኖሩ መካ​ከ​ልም ወንድ ያላ​ወቁ አራት መቶ ቆነ​ጃ​ጅት ደና​ግ​ልን አገኙ፤ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሴሎ ወደ ሰፈሩ አመ​ጡ​አ​ቸው።


በዚ​ያም ጊዜ የብ​ን​ያም ልጆች ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሴቶች ያዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን ሴቶች ሰጡ​አ​ቸው። በዚ​ህም ተስ​ማሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos