Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 20:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “በአንዲት ከተማ ላይ አደጋ ለመጣል በምትዘምትበት ጊዜ በመጀመሪያ እንዲገብሩ የሰላም ድርድር ጠይቅ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፣ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምትበት ጊዜ፥ አስቀድመህ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ለመ​ዋ​ጋት ወደ አን​ዲት ከተማ በደ​ረ​ስህ ጊዜ አስ​ቀ​ድ​መህ በሰ​ላም ቃል ጥራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለመዋጋት ወደ አንዲት ከተማ በደረስህ ጊዜ አስቀድመህ በዕርቅ ቃል ጥራቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 20:10
13 Referencias Cruzadas  

በሩቅና በቅርብ ላሉትም ሁሉ ሰላም ይሁን! እኔ ሕዝቤን እፈውሳለሁ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሠረገሎችን ከእስራኤል፥ የጦር ፈረሶችንም ከኢየሩሳሌም አስወግዳለሁ፤ የጦር ቀስቶችን እሰባብራለሁ፤ ንጉሥሽ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲኖር ያደርጋል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርና ከታላቁ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሆናል።”


እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።


ይህም ሁሉ የሆነው እኛን ከራሱ ጋር በክርስቶስ አማካይነት ባስታረቀንና የማስታረቅንም አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው።


መጥቶም ለእናንተ ርቃችሁ ለነበራችሁትና ቀርበው ለነበሩት ለአይሁድም የሰላምን የምሥራች ቃል ሰበከ።


“ከዚህም በኋላ የሰላም መልእክት የያዙ መልእክተኞችን ከቅዴሞት በረሓ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሲሖን እንዲህ ስል ላክሁ፤


የቅጽር በሮቻቸውን ከፍተው እንዲገብሩ የሰላም ድርድርህን ቢቀበሉ በከባድ ሥራ ያገልግሉህ።


የጦር መሪዎቹ ለሠራዊቱ ይህን ተናግረው ከጨረሱ በኋላ ለእያንዳንዱ ክፍል አዛዦችን ይምረጡ።


ከዚህ በኋላ ዮፍታሔ ወደ ዐሞን ንጉሥ መልእክተኞችን ልኮ “ከእኛ ጋር የተጣላህበት ምክንያት ምንድን ነው? አገራችንንስ የወረርከው ለምንድነው?” ብለው እንዲጠይቁት አደረገ።


ከዚህ በኋላ መላው ጉባኤ የሪሞን አለት ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ወደነበሩት ብንያማውያን መልእክት ልከው ጦርነቱ እንዲቆም ተስማሙ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos