ዘዳግም 19:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈራጆቹም አጥብቀው ይመረምራሉ፤ ያም ምስክር ሐሰተኛ ምስክር ሆኖ በወንድሙ ላይ በሐሰት ተናግሮ ቢገኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈራጆችም ጕዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፤ ያም ምስክር በወንድሙ ላይ በሐሰት የመሰከረ መሆኑ ከተረጋገጠ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈራጆችም ጉዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፤ ያም ምስክሩ በወንድሙ ላይ የሐሰት ክስ አቅርቦ ከተገኘ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳኞቹ ጉዳዩን በጥብቅ ይመረምራሉ፤ ያም ሰው እስራኤላዊ በሆነው ወገኑ ላይ የሐሰት ክስ አቅርቦ ከተገኘ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈራጆቹም አጥብቀው ይመረምራሉ፤ ያም ምስክር ሐሰተኛ ምስክር ሆኖ በወንድሙ ላይ በሐሰት ተናግሮ ቢገኝ፥ |
ትፈልጋለህ ትመረምራለህም፤ ትጠይቃለህም፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከልህ እንደ ተደረገ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥
ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥