La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 18:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት፥ ለሌ​ዊም ነገድ ሁሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ድር​ሻና ርስት አይ​ኑ​ራ​ቸው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ር​በው መሥ​ዋ​ዕት ድር​ሻ​ቸው ነው፤ እር​ሱን ይመ​ገ​ባሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሌዋውያን ካህናት፣ የሌዊ ነገድም ሁሉ ከእስራኤል ጋራ የመሬት ድርሻ ወይም ርስት አይኖራቸውም፤ ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው መባ ይብሉ፤ ድርሻቸው ነውና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ሌዋውያን ካህናት፥ የሌዊ ነገድም ሁሉ ከእስራኤል ጋር የመሬት ድርሻ ወይም ርስት አይኖራቸውም፤ ድርሻቸው ነውና ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው መባ ይብሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሌዋውያን ካህናት፥ እንዲያውም፥ መላው የሌዊ ነገድ ከቀሩት የእስራኤል ነገዶች ጋር የርስት ድርሻ የላቸውም፤ በዚህ ምትክ ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕትና መባ እየተመገቡ ይኖራሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሌዋውያን ካህናት፥ ለሌዊም ነገድ ሁሉ ከእስራኤል ጋር ድርሻና ርስት አይሆንላቸውም፤ በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕቱንና ርስቱን ይበላሉ።

Ver Capítulo



ዘዳግም 18:1
12 Referencias Cruzadas  

የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ሠዋ ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ዘንድ በእኔ ፊት አይ​ታ​ጣም።”


“ርስት አይ​ሆ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘንድ ርስት አት​ስ​ጡ​አ​ቸው፤ እኔ ርስ​ታ​ቸው ነኝ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “በም​ድ​ራ​ቸው ርስት አት​ወ​ር​ስም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ድርሻ አይ​ሆ​ን​ል​ህም፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ህና ርስ​ትህ እኔ ነኝ።


ከአ​ንድ ወርም ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ ወን​ዶች ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል ርስት አል​ተ​ሰ​ጣ​ቸ​ው​ምና ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር አል​ተ​ቈ​ጠ​ሩም።


ስለ​ዚህ ለሌ​ዋ​ው​ያን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ጋር ክፍ​ልና ርስት የላ​ቸ​ውም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና።


በም​ድ​ርህ ላይ በም​ት​ኖ​ር​በት ዘመን ሁሉ ሌዋ​ዊ​ዉን ቸል እን​ዳ​ትል ተጠ​ን​ቀቅ።


ለሌዊ ነገድ ግን ርስት አል​ተ​ሰ​ጠም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስ​ታ​ቸው ነውና፥ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሞ​ዓብ ሜዳ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዳ​ካ​ፈ​ላ​ቸው እን​ዲሁ ተካ​ፈሉ።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክህ​ነት ርስ​ታ​ቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እድል ፋንታ የላ​ቸ​ውም፤ ጋድም፥ ሮቤ​ልም፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ሥ​ራቅ በኩል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ርስ​ታ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋል።”