የሌዋዊውም የይምላእ ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ሕዝቡ በፈቃዳቸው ለእግዚአብሔር በአቀረቡት ላይ ተሾመ።
ዘዳግም 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ቀዳምያታችሁን፥ ስዕለታችሁንም፥ በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኵራት ውሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፣ ዐሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፣ ስእለቶቻችሁንና የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን፣ የቀንድ ከብት መንጋችሁን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ ስእለቶቻችሁንና የፈቃዳችሁን ስጦታዎች፥ የከብት መንጋችሁን እና የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አቅርቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትንና የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን፥ የከብቶቻችሁንና የበጎቻችሁን በኲር ታቀርባላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላ መሥዋዕታችሁንም፥ አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቍርባን፥ ስእለታችሁንም፥ በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኵራት ውሰዱ። |
የሌዋዊውም የይምላእ ልጅ የምሥራቁ ደጅ በረኛ ቆሬ የእግዚአብሔርን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያካፍል ሕዝቡ በፈቃዳቸው ለእግዚአብሔር በአቀረቡት ላይ ተሾመ።
እግዚአብሔርም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው፥ “ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንም ስፍራ ለራሴ ለመሥዋዕት ቤት መርጫለሁ።
የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ ወንድሞቹም ካህናቱ፥ የሰላትያልም ልጅ ዘሩባቤል፥ ወንድሞቹም ተነሥተው በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡበት ዘንድ የእስራኤልን አምላክ መሠዊያ ሠሩ።
በሕጉም እንደ ተጻፈ የልጆቻችንንና የእንስሶቻችንን በኵራት፥ የበሬዎቻችንንና የበጎቻችንን በኵራት በአምላካችን ቤት ወደሚያገለግሉት ካህናት ወደ አምላካችን ቤት እናመጣ ዘንድ፥
የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን፥ የዘይቱንም ቀዳምያት፥ የመቅደሱን ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት፥ በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፤ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።
“በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው ለዘለዓለም ይገዙልኛል፤ በዚያም እቀበላችኋለሁ፤ በዚያም ቀዳምያታችሁን፥ በኵራታችሁንም፥ የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ እጐበኛለሁ።
“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።
የእንስላልና የጤና አዳም፥ ከአትክልትም ሁሉ ዐስራት የምታገቡ ፍርድንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ቸል የምትሉ እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ይህንም ልታደርጉ ይገባችኋል፥ ያንም አትተዉ።
የእህልህን፥ የወይን ጠጅህን፥ የዘይትህንም ዐሥራት፥ የላምህንና የበግህንም በኵራት፥ የተሳልኸውንም ስእለት ሁሉ፥ በፈቃድህ ያቀረብኸውን፥ የእጅህንም ቀዳምያት በከተሞችህ ሁሉ ውስጥ መብላት አትችልም።
አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ፍሬ ሁሉ ቀዳምያት ውሰድ፤ በዕንቅብም አድርገው፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደ መረጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።
ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል፥ ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቍርባን፥ በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ በእግዚአብሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።
ሰውዬውም ሕልቃና ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር የዓመቱን መሥዋዕትና ስእለቱን፥ የምድሩንም ዐሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር ያቀርብ ዘንድ ወጣ።
እርስዋም ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ እንጀራ፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴሎም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት ገባች። ልጃቸውም ከእነርሱ ጋር ነበረ።