ዘዳግም 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፤ ጽላቱንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከተራራው ተመልሼ ወረድሁ፤ እግዚአብሔር ባዘዘኝ መሠረት በሠራሁት ታቦትም ውስጥ፣ ጽላቱን አስቀመጥኋቸው፤ አሁንም እዚያ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፥ ጌታም እንዳዘዘኝ በዚያ ይገኛሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ከተራራው ተመልሼ በመውረድ እግዚአብሔር ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን በሠራሁት ታቦት ውስጥ አኖርኳቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እነሆ፥ በዚያው ውስጥ ይገኛሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ። |
ሙሴም ተመለሰ፤ ሁለቱንም የምስክር ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ የድንጋይ ጽላቱም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።
በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም። በጽላቱም ዐሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ሁለቱ ጽላት በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር ፊቱ እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር።
ሙሴም ጽላቱን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አኖረው፤ መሎጊያዎቹንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አደረገ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረው።
በሰበርሃቸው በፊተኞቹ ጽላት የነበሩትን ቃሎች ሁሉ በእነዚህ ጽላት እጽፋለሁ፤ በታቦቱም ውስጥ ታደርጋቸዋለህ አለኝ።
ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።