ዘዳግም 1:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ተራራማ አገር ይኖሩ የነበሩ አሞሬዎናውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ንብ እንደምትነድፍም ነደፉአችሁ፤ አሳደዱአችሁም፤ ከሴይር እስከ ሔርማም ድረስ መቱአችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚያ በተራራማው አገር የሚኖሩት አሞራውያን ሊወጓችሁ ወጡ፤ እንደ ንብ ሰራዊትም ሆነው አባረሯችሁ፤ ከሴይር አንሥቶ እስከ ሖርማ ድረስ አሳድደው መቷችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ እንደ ንብ መንጋ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር ድል ነሷችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነዚያ ኮረብታዎች ላይ የሚኖሩ አሞራውያንም መጥተው ተጋጠሙአችሁ፤ ሠራዊታቸውም እንደ ንብ መንጋ ግር ብለው መጥተው እስከ ሆርማ ድረስ አሳደዱአችሁ፤ ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም አገርም ድል አደረጉአችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም በተራራማው አገር ይኖሩ የነበር አሞራውያን ወጥተው ተጋጠሙአችሁ፥ ንብ እንደምታሳድድም አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ። |
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በግብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝንብ፥ በአሦርም ሀገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል።
በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፤ መትተዋቸውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳደዱአቸው። ወደ ከተማም ተመለሱ።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፤ ከነዓናውያንንም አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ እነርሱንም፥ ከተሞቻቸውንም ሕርም ብለው አጠፉአቸው፤ የዚያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።
“እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፤ በሰባት መንገድም ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ የተበተንህ ትሆናለህ።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
የጋይ ሰዎችም ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ሰዎችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀምረው እስከ አጠፉአቸው ድረስ አባረሩአቸው፤ በቍልቍለቱም ገደሉአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ደነገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።