ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
ቈላስይስ 3:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ዋጋችሁን እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁ፤ ለክርስቶስ ትገዛላችሁና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጌታ ዘንድ እንደ ብድራት የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንንም ስታደርጉ ከጌታ የርስትን ሽልማት እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለዚህም ጌታ ሰማያዊ ርስትን ዋጋ አድርጎ እንደሚሰጣችሁ ታውቃላችሁ፤ የምታገለግሉትም ጌታ ክርስቶስን ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። |
ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”
“ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
አሁንም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካምም አድርጉላቸው፤ እንዲመልሱላችሁ ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ ዋጋችሁም ብዙ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለበጎዎችና ለክፉዎች ቸር ነውና።
እኔን የሚያገለግለኝ ካለ ይከተለኝ፤ የሚያገለግለኝ እኔ ባለሁበት በዚያ ይኖራልና፤ እኔን የሚያገለግለኝንም አብ ያከብረዋል።
አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፥ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማስተማር ተለይቶ ከተጠራ ሐዋርያ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከሚሆን ከጳውሎስ፥
ከእግዚአብሔር እንደ ተማርሁ አስተምሬአችኋለሁና፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱን ራሱን በያዙባት በዚያች ሌሊት ኅብስቱን አነሣ።
አሁንስ ለእግዚአብሔር ያይደለ ለሰው ብዬ አስተምራለሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰኛለሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወድስ የክርስቶስ ባሪያ አይደለሁም።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሮች እንጂ ለሰው ደስ እንደሚያሰኝ ለታይታ አይደለም።
በመታለልና ራስን ዝቅ በማድረግ ለመላእክት አምልኮ ትታዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአላየውም በከንቱ የሥጋው ምክር እየተመካ የሚያሰንፋችሁ አይኑር።
ያለ እምነትም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሰው አስቀድሞ እግዚአብሔር እንዳለ፥ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጣቸው ሊያምን ይገባዋል።
ስለዚህ ኢየሱስ ሞትን ተቀብሎ፥ በቀደመው ሥርዐት ስተው የነበሩትን ያድናቸው ዘንድ ወደ ዘለዓለም ርስቱም የጠራቸው ተስፋውን ያገኙ ዘንድ፥ ለአዲሲቱ ኪዳን መካከለኛ ሆነ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ፤
እግዚአብሔር እንደ ሥራሽ ይስጥሽ፣ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት።