አሞጽ 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድራቸውም እተክላቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም” ይላል ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር አምላክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤልን በገዛ ምድራቸው እተክላቸዋለሁ፤ ከሰጠኋቸውም ምድር፣ ዳግመኛ አይነቀሉም፤” ይላል አምላክህ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድራቸውም ላይ እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥” ይላል ጌታ አምላክህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤን እስራኤልን በሰጠኋቸው ምድር ላይ እተክላቸዋለሁ፤ ዳግመኛም ከዚያ ተነቅለው አይወጡም፤” ይህን የሚናገር እግዚአብሔር አምላካችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድራቸውም እተክላቸዋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ከሰጠኋቸው ከምድራቸው አይነቀሉም፥ ይላል አምላክህ እግዚአብሔር። |
ነገር ግን፥ “የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር፥ ከተሰደዱበትም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።
ነገር ግን፥ “የእስራኤልን ቤት ዘር ከሰሜን ሀገርና ካሳደዷቸውም ሀገር ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን!” ይባላል፤ በምድራቸውም መልሶ ያኖራቸዋል።
ዐይኔንም ለበጎነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ወደዚህችም ምድር ለመልካም እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።
በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል፤ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
እነሆ በቍጣዬና በመዓቴ፥ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት ሀገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤
ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ይቅር እላቸዋለሁ፤ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
እንግዲህ ለአሕዛብ ንጥቂያ አይሆኑም፤ የምድርም አራዊት አይበሉአቸዋም፤ ተዘልለውም ይቀመጣሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የእስራኤልን ልጆች ከገቡባቸው ከአሕዛብ መካከል እወስዳለሁ፤ ከስፍራም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣቸዋለሁ፤
አባቶቻችሁም በኖሩባት፤ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው፥ የልጅ ልጆቻቸውም ለዘለዓለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም ዳዊት ለዘለዓለም አለቃ ይሆናቸዋል።