Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 32:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት፣ የዕርሻ ቦታና የወይን አትክልት ስፍራ እንደ ገና ይገዛሉ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደገና ይገዛሉ።’”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እንደገና በዚህች ምድር ቤቶችን፥ የእርሻ መሬቶችን፥ የወይን ተክል ቦታዎችን መግዛት የሚቻልበት ጊዜ ይመጣል ብሎአል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 32:15
13 Referencias Cruzadas  

በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የያ​ዕ​ቆ​ብን ድን​ኳን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም እራ​ራ​ለሁ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በጕ​ብ​ታዋ ላይ ትሠ​ራ​ለች፤ አዳ​ራ​ሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖ​ሪያ ይሆ​ናል።


እነሆ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍቴ እነ​ር​ሱን ካሳ​ደ​ድ​ሁ​ባት ሀገር ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም እን​ዲ​ኖሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤


በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በሀ​ገሩ ሁሉ ከገ​በ​ሬ​ዎ​ችና መን​ጋን ይዘው ከሚ​ዞሩ ጋር የሚ​ኖሩ ሰዎች ይገ​ኛሉ።


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


እንደ ገናም በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ የወ​ይን ተክ​ሎ​ችን ትተ​ክ​ሊ​አ​ለሽ፤ የም​ት​ተ​ክሉ ትከሉ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤


የባ​ር​ያ​ውን ቃል ያጸ​ናል፤ የመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ምክር ይፈ​ጽ​ማል። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ኛ​ለሽ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ትታ​ነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ምድረ በዳ​ዎ​ች​ዋም ይለ​መ​ል​ማሉ፤” ይላል፤


“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ብዙ ቀን ይጠ​በቅ ዘንድ የታ​ተ​መ​ውን ይህን የውል ወረ​ቀት ወስ​ደህ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ አኑ​ረው።


ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ወይ​ኑ​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በአሉ በሚ​ን​ቋ​ቸው ሁሉ ላይ ፍር​ድን በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ ተዘ​ል​ለው ይቀ​መ​ጣሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


አን​ተም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እር​ሻ​ውን በብር ግዛ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጥራ አል​ኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተ​ምሁ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ምሁ፤ ከተ​ማ​ዪቱ ግን ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios