ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
አሞጽ 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞጽም መልሶ አሜስያስን አለው፥ “እኔ ላም ጠባቂና በለስ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞጽም ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እረኛና የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞጽም ለአሜስያስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ እኔ የመንጋዎች ጠባቂና የወርካ ዛፎችን ተንከባካቢ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሞጽም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ እኮ የመንጋዎች እረኛና የሾላ ፍሬ ተንከባካቢ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞጽም መልሶ አሜስያስን አለው፦ እኔ ላም ጠባቂና ወርካ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፥ |
ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
በኢያሪኮም የነበሩት የነቢያት ልጆች ኤልሳዕ ወደ እነርሱ ሲመጣ ባዩት ጊዜ፥ “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፎአል” አሉ። ሊገናኙትም መጥተው በፊቱ በምድር ላይ ሰገዱለት።
በቤቴልም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ መጥተው፥ “እግዚአብሔር ጌታህን ከአንተ ለይቶ ዛሬ እንደሚወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፥ “አዎን፥ ዐውቄአለሁ፤ ዝም በሉ” አላቸው።
ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ በኢያሪኮም የነበሩ የነቢያት ልጆች ወደ ኤልሳዕ ቀርበው፥ “እግዚአብሔር ጌታህን ከራስህ ላይ ዛሬ እንዲወስደው ዐውቀሃልን?” አሉት። እርሱም፥ “አዎን፥ ዐውቄአለሁ፤ ዝም በሉ” አላቸው።
ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልጌላ ተመለሰ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ኤልሳዕም ሎሌውን፥ “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብስልላቸው” አለው።
በዚያን ጊዜም ነቢዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “በሶርያ ንጉሥ ታምነሃልና፥ በአምላክህም በእግዚአብሔር አልታመንህምና ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ ጭፍራ ከእጆችህ አምልጠዋል።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።
የቀረውም የፊተኞቹና የኋለኞቹ የኢዮሣፍጥ ነገሮች፥ እነሆ የእስራኤልን ነገሥታት ታሪክ በጻፈው በአናኒ ልጅ በነቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽፈዋል።
እየዞሩ የሚለምኑና የሚበሉ በቅልውጥም የሚኖሩ ወራዶች፥ ዐመፀኞችና ከበጎ ነገሮች ሁሉ የተቸገሩ ናቸው። ከታላቅ ረኃብም የተነሣ ጨው ጨው የሚለውን የእንጨት ሥር ይበላሉ።
በቴቁሔ በላም ጠባቂዎች መካከል የነበረ አሞጽ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከሆነበት ከሁለት ዓመት በፊት ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ቃል ይህ ነው።
ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ሊያሳፍር የዚህን ዓለም ሰነፎች መረጠ፤ ኀይለኞችንም ያሳፍር ዘንድ እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ደካሞች መረጠ።
ቀድሞም የሚያውቁት ሁሉ በነቢያት መካከል ባዩት ጊዜ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው፥ “በቂስ ልጅ ላይ የሆነው ምንድን ነው? በውኑ ሳኦል ከነቢያት ወገን ነውን?” ተባባሉ።