ኢዮብ 30:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እየዞሩ የሚለምኑና የሚበሉ በቅልውጥም የሚኖሩ ወራዶች፥ ዐመፀኞችና ከበጎ ነገሮች ሁሉ የተቸገሩ ናቸው። ከታላቅ ረኃብም የተነሣ ጨው ጨው የሚለውን የእንጨት ሥር ይበላሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ከቍጥቋጦ ምድር ጨው ጨው የሚል አትክልት ለቀሙ፤ ምግባቸውም የክትክታ ሥር ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በቁጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚለውን ቅጠላ ቅጠል ይቀጥፋሉ፥ እንዲሞቃቸውም የክትክታ ሥር ይበላሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ጨው ጨው የሚሉ የበረሓ ቅጠላ ቅጠሎችን ይለቅሙ ነበር፤ ጣዕም የሌላቸውንም የክትክታ ሥሮች ይበሉ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በቍጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚለውን አትክልት ይለቅማሉ፥ የክትክታ ሥር ደግሞ መብላቸው ነው። Ver Capítulo |