አሞጽ 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ከአለቆቻቸው አስቀድመው ይማረካሉ፤ ሯጮች የሚሆኑ የኤፍሬም ፈረሶችም ያልቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናችሁ፤ መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በመጀመሪያ ተማርከው ከሚፈልሱት ይሆናሉ፥ እንደ ፈቃዳቸው ከሚሆኑ መካከል ፈንጠዝያ ይርቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ተማርካችሁ በመሄድ እናንተ የመጀመሪያዎቹ ትሆናላችሁ፤ በዚያን ጊዜ የዚያ የቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ ኑሮአችሁ ፍጻሜ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በምርኮ መጀመሪያ ይማረካሉ፥ ተደላድለው ከተቀመጡትም ዘንድ ዘፈን ይርቃል። |
የከበሮአቸው ደስታ አልቆአል፤ መታጀራቸውም አልቃለች፤ የኃጥኣን ሀብት አልቆአል፤ የመሰንቆ ድምፅም ቀርቶአል።
“ዕራቁታችሁን ያወጡአችኋል፤ እርስ በርሳችሁም ትተያያላችሁ፤ በሬማንም ተራራ ትጣላላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፤ ወደ ጌልገላም አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።”
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”
በሰይፍ ስለት ይወድቃሉ፤ በአሕዛብም ሁሉ ይማረካሉ፤ የአሕዛብ ጊዜያቸው እስኪፈጸም ድረስ አሕዛብ ኢየሩሳሌምን ይረግጡአታል።