ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።
አሞጽ 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉ ቀንን ለሚፈልጓት፥ የሐሰት ሰንበታትን ለሚያቀራርቡና አንድ ለሚያደርጉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣ የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉውን ቀን ከእናንተ ታርቃላችሁን? የግፍንስ ወንበር ታቀርባላችሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ “ክፉ ቀን ፈጥኖ አይመጣም” ብላችሁ በማሰብ በአስተዳደራችሁ የግፍን ሥራ ታፋጥናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉውን ቀን ከእናንተ ለምታርቁ፥ የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ፥ |
ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።
አንቺም፥ “እኔ ለዘለዓለም እመቤት እሆናለሁ” ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላሰብሽም፤ ፍጻሜውንም አላስታወስሽም።
ኑ፤ የወይን ጠጅ እንውሰድ፤ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፤ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።
“የሰው ልጅ ሆይ! ዐመፀኛው የእስራኤል ቤት፦ ይህቺ የሚያያት ራእይ ለብዙ ዘመን ናት፤ እርሱም ለሩቅ ወራት ትንቢትን ይናገራል” ይላሉ።
የበገናውን አውታር ድምፅ ይቃኛሉ፤ ከብዙ ሰዎችም ጉባኤ ጋር ሰካራሞቹ ከምድረ በዳ መጡ፤ በእጃቸው አንባር፥ በራሳቸውም የተዋበ አክሊል አደረጉ።
በፋርስ ሀገሮችና በግብፅ ሀገሮች ዐውጁና፥ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ተአምር፥ በመካካልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ” በሉ።
ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኀጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ ዐውቃለሁና።
የእግዚአብሔርን ቀን ለምትፈልጉ ወዮላችሁ! የእግዚአብሔርን ቀን ለምን ትፈልጋላችሁ? ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይደለም።
ፍርድን ወደ ቍጣ፥ የእውነትንም ፍሬ ወደ እሬት ለውጣችኋልና፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?