ሐዋርያት ሥራ 8:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያነበው የነበረ የመጽሐፉ ቃልም እንዲህ የሚል ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንዲሁ አፉን አልከፈተም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጃንደረባው ያነብብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል የሚከተለው ነበረ፦ “እርሱ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ነበረ፤ ሲሸልቱትም ዝም እንደሚል ጠቦት፤ እርሱም ለመናገር አፉን አልከፈተም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያነበውም የነበረ የመጽሐፉ ክፍል ይህ ነበረ፤ እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፥ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። |
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን ኣያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ፤ በልብሱም ላይ ዕጣ ተጣጣሉና ተካፈሉ።
በማግሥቱም ዮሐንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታችን ኢየሱስን አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።
ጃንደረባውም፥ “ያስተማረኝ ሳይኖር በምን አውቀዋለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረገላውም ወጥቶ አብሮት ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።