ሐዋርያት ሥራ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም እጃቸውን ጫኑባቸው፤ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ እነርሱም መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ፥ እጆቻቸውን በጫኑባቸው ጊዜ ሰዎቹ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ። |
ሌዋውያንንም በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው፤ የእስራኤልም ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው።
ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደ፤ ያንጊዜም በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ።
ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ ይናገሩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንደ አደላቸው መጠንም እየራሳቸው በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመሩ።
ያንጊዜም ሐናንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁንም ጫነበትና፥ “ወንድሜ ሳውል፥ በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታይና መንፈስ ቅዱስ ይመላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል” አለው።