በደሴቲቱም ሁሉ ሲዘዋወሩ ጳፉ ወደምትባል ሀገር ደረሱ፤ በዚያም አንድ አይሁዳዊ የሆነ ሐሰተኛ ነቢይና አስማተኛ ሰው አገኙ፤ ስሙም በርያሱስ ይባላል።
ሐዋርያት ሥራ 28:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ በደኅና በደረስን ጊዜ ደሴቲቱ መላጥያ እንደምትባል ዐወቅን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደኅና ወደ ምድር ከደረስን በኋላ፣ ደሴቲቱ መላጥያ ተብላ እንደምትጠራ ተረዳን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደኅና ከደረስን በኋላ በዚያን ጊዜ ደሴቲቱ መላጥያ እንደምትባለ አወቅን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ምድር በደኅና ከደረስን በኋላ የደረስንባት ደሴት ማልታ የምትባል መሆንዋን ዐወቅን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደኅና ከደረስን በኋላ በዚያን ጊዜ ደሴቲቱ መላጥያ እንድትባል አወቅን። |
በደሴቲቱም ሁሉ ሲዘዋወሩ ጳፉ ወደምትባል ሀገር ደረሱ፤ በዚያም አንድ አይሁዳዊ የሆነ ሐሰተኛ ነቢይና አስማተኛ ሰው አገኙ፤ ስሙም በርያሱስ ይባላል።
ራእዩንም ባየ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ልንሄድ ወደድን፤ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር የሚጠራን መስሎናልና።
ከዚህም በኋላ ፊስጦስ ወደ ቄሣር ወደ ኢጣልያ በመርከብ እንሄድ ዘንድ ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስ ከሌሎች እስረኞች ጋር አብሮ የአውግስጦስ ጭፍራ ለነበረ ዩልዮስ ለሚባል የመቶ አለቃ ተሰጠ።
በነጋ ጊዜም ቀዛፊዎች ቦታውን አልለዩም፤ የሚሄዱበትንም አላወቁም፤ ነገር ግን ለባሕሩ አቅራቢያ የሆነውን የደሴት ተራሮች አዩ፤ መርከባቸውንም ወደ እዚያ ሊያስጠጉ ፈለጉ።
የቀሩትም በመርከቡ ስብርባሪ ዕንጨትና በሳንቃው ላይ ተሻገሩ፤ ሌሎችም በመርከቡ ገመድ ላይ እየተንጠላጠሉ ተሻገሩ፤ ሁሉም እንዲህ ባለ ሁኔታ በደኅና ወደ ምድር ደረሱ።