ሐዋርያት ሥራ 27:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ቀንም ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንም ሳናይ ማዕበሉ ጸናብን፤ ለመዳንም ተስፋ ቈርጠን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ቀን፣ ፀሓይንም ከዋክብትንም ማየት ስላልተቻለና ነፋስ ስለ በረታብን፣ ለመትረፍ የነበረን ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ቀንም ፀሐይን ከዋክብትንም ሳናይ ትልቅ ነፋስም ሲበረታብን ጊዜ፥ ወደ ፊት እንድናለን የማለት ተስፋ ሁሉ ተቆረጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለብዙ ቀን ፀሐይም ሆነ፤ ከዋክብት ስላልታዩና ነፋሱም እየበረታብን ስለ ሄደ ከእንግዲህ ወዲህ መዳን አንችልም ብለን ተስፋ ቈረጥን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ቀንም ፀሐይን ከዋክብትንም ሳናይ ትልቅ ነፋስም ሲበረታብን ጊዜ፥ ወደ ፊት እንድናለን የማለት ተስፋ ሁሉ ተቈረጠ። |
በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፤ ዳግመኛም ጕልበት እያለኝ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን መንገድ አልተውም አላልሽም፤ ይህንም ስላደረግሽ አላፈርሽም።
እግርሽን ከሰንከልካላ መንገድ፥ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ እርስዋ ግን፥ “እጨክናለሁ፤ እንግዶችንም ወድጄአለሁ” ብላ ተከተለቻቸው።
እግዚአብሔርም ተናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።
እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፤ በባሕሩም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፤ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።
ከእኛም መብል የበላ አልነበረም። ጳውሎስም ተነሥቶ በመካከል ቆመና እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰምታችሁኝ ቢሆን ከቀርጤስም ባትወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳትና መከራ በዳናችሁ ነበር።
ሦስት ጊዜ በበትር ደበደቡኝ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ መቱኝ፤ መርከቤ ሦስት ጊዜ ተሰበረች፤ በጥልቁ ባሕር ውስጥ ስዋኝ አድሬ፥ ስዋኝ ዋልሁ።
ያንጊዜ ክርስቶስን አታውቁትም ነበር፤ ከእስራኤል ሕግ የተለያችሁ ነበራችሁ፤ ከተስፋው ሥርዐትም እንግዶች ነበራችሁ፤ ተስፋም አልነበራችሁም፤ በዚህም ዓለም እግዚአብሔርን አታውቁትም ነበር።